የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት በመደ ወላቡ ወረዳ ለወላቡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው አጋዥ ቱቶሪያልና ስልጠና ተጠናቀቀ።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት በመደ ወላቡ ወረዳ ለወላቡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንና ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው አጋዥ ቱቶሪያልና ስልጠና ተጠናቀቀ።

**********************************************

(ባሌ-ሮቤ ህዳር 23/2018 ዓ.ም. መወዩ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)

የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ መምህራን በማህበረሰብ አገልግሎት ሽፋን በዩኒቨርስቲው የሲያሜው ስፍራ በሆነው ምስራቅ ቦረና ዞን በመደ ወላቡ ወረዳ ለወላቡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመምህራንና ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው አጋዥ ቱቶሪያልና ስልጠና ተጠናቋል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎቱን በማጠናከር በምስራቅ ቦረና ዞን በመደ ወላቡ ወረዳ በብድሬ ከተማ በሚገኘው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ በ 11 መምህራን ተግዞ ተማሪዎችን በሒሳብ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ፣ በባዮሎጂ፣ በጂኦግራፊ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በታሪክ የትምህርት አይነቶች በተከታታይ ለ5 ቀናት ለ169 ተማሪዎች የትምህርት ክለሳና ከዚህ በፊት የተሰጡ የፈተናዎችን ጥያቄ በመስራት ተማሪዎች ለፈተና የሚያደርጉትን ዝግጅት መደገፍ ችሏል።

ከዚሁ ጎን ለጎን 50 ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት አመራሮች “Educational Assessment, Evaluation and Feedback” እና “Educational Technology” በሚል ርዕስ ዙርያ ለተከታታይ 3 ቀን በዩኒቨርስቲው ባለሙያ አጭር የስራ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

የቱቶሪያል ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ባገኙት ዕድል ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፣ ለበለጠ ዝግጅት እንደሚያነቃቸው ተናግረዋል። ስልጠናውን ያገኙ መምህራን በበኩላቸው ያገኙት ስልጠና የጎደላቸውን የክህሎትና ሁለገብ የምዘና ስርዓት ለማሳለጥ እንደሚረዳቸው ተናግረዋል።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት