መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ “Thematic Research Proposal, Training and Project Evaluation Orientation “በሚል መሪ ሃሳብ ለመምህራን እና ለተመራማሪዎች ስልጠና ሰጠ፡፡
**********************************
(ባሌ-ሮቤ ህዳር 11/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ “Thematic Research Proposal, Training and Project Evaluation Orientation “በሚል መሪ ሃሳብ ከተለያዩ ኮሌጆች እና ካምፓሶች ለተውጣጡ ለመምህራን እና ተመራማሪዎች ነው ስልጠናውን እየሰጠ ያለው፡፡
ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ቴክኖሎጅ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ ስልጠናውን አስመልክተው እንዳሉት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በርካታ የምርምር ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ሆኖም ቀደም ሲሉ ሲሰሩ የነበሩት የምርምር ስራዎች በተበጣጠሰ መልኩ እንደነበር በማንሳት አሁን ላይ በኢ.ፌ.ድ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በተቀመጠልን አቅጣጫ መሰረት ጥናትና ምርምር ሰራዎች እንደየዘርፉ ቅርርብነት በጋራ በመሆን እና የተለያዩ መስኮች ባካተተ መልኩ ምርምሮች ሊሰሩ እንደሚገቡ እንዲሁም የሚሰሩ የምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን/ ብሔራዊ ችግሮችን የሚፈቱ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በመሆኑም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራኑ እና ተመራማሪዎቹ ስለ ቴማቲክ ሪሰርች/ Thematic Research/ ስልጠና በመስጠት ግንዛቤ ማስጨበጥን አላማ ያደረገ ስልጠና እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
“Thematic Research and Evaluation Process’’ በሚል ርእስ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምርምር ህትመት እና ስነ ምግባር ስርፀት ዳይሬክተር በሆኑት በዶ/ር አዲሱ አሰፋ እንዲሁም “Training Project Evaluation Process” በሚል ርእስ በዓለም አቀፍ የምርምር አጋርነት ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ አባተ ፅሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት








