በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ቢሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ::
(ባሌ-ሮቤ ህዳር 25/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ቢሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዲሞክራሳዊ መግባባት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ::
በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፐሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፤ ይህን በዓል ስናከብር በሀገራችን ውስጥ ያሉ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በጋራ የመሰረቷትን ትልቋን ኢትዮጵያ በጋራ ለመዘከር እና ልዩነቶቻችን ውበታችን መሆኑን ለመመስክር ነው ብለው፡፡ የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ከሀገረ ምስረታ ጀምሮ አሁን እስከ ደረስንበት የለውጥ ጎዳና ትልቅ አስተዋፆ እንዳለቸው ተናግረዋል፡:
በበዓሉ ላይ የዕለቱን ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት በውጪ ጉዳይ ሚኒስተር የውጪ ጉዳይ ጥናት ኢንስተቲዩት ተመራማሪ አቶ ደበላ ፊጡማ፤ ኢትዮጵያ በበርካታ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የተገመደች ሀገር መሆኗ እጂግ የሚያኮራት የውበትና መቻቻል ተምሳሌት መፍለቅያ አድርጓታል ብለው፤እዚህም እዚያም አንዳንድ አፍራሽ ሀይሎች የሚያሰራጩትን ወሬ ሳንሰማ፤ለውጥን በመደገፍ የለውጡን ጎዳና መከተል ከሁም ዜጋ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል፡፡
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በአንድ ቦታ ከሚገኙበት አንዱ መሆኑን ያነሱት ደግሞ በበዓሉ ላይ የውይይት የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ዜጋ እና ሥነ-ምግባር ትምህርት ክፍል መምህር ከሚል ከድር፤ ልዩነቶቻችንን በማክበር፤ አሮጌውን ትርክት በማደስ የኢትዮጵያን ብልፅግና ልዕልና ከፍ ማድረግ የሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ኃለፊነት ነው ብለዋል፡፡
በበዓሉ ላይ በመገኘት የበዓሉ ድምቀት ከነበሩ ያናገርናቸው አንዳንድ ተማሪዎች እናደገለፁት 20ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓልን በዚህ መልክ ማክበራችን እኛ ተማሪዎች ይበልጥ እንድንቀራረብ በማድረግ፤ ወዳጅነታችንንና አንድነታችንን ያጎላዋል ብለዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት











