የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በስንዴ ምርታማነት ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በስንዴ ምርታማነት ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

**************************************************************

(ባሌ-ሮቤ ህዳር 23/2018 መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)

የመደ ወላቡ የኒቨርሲቲ “የስንዴ ምርታማነት ለግብርናችን እምርታ”በሚል መሪ ቃል በስንዴ ምርታማነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሃደ።

በውይይት መድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው በግብርና ምርታማነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ በርካታ ስራዎች በጥናትና ምርምር ተደግፈው የቀረቡ ሲሆን፤ በመስክ ጉብኝት በዩኒቨርስቲው የሚደገፉ በሦሥቱ ዞኖች ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ከስምንቱ የስንዴ የኩታ ገጠም እርሻዎች መካከል በሲናና ወረዳ ሻሎ ቀበሌ እና አጋርፋ ወረዳ አሊ ቀበሌ ተጎብኝተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በግብርና ላይ እየሰራ ያለውን ስራ ይበልጥ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና፤ ግብርናችንን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከግብርና ባለድርሻ አካላት ጋር በይበልጥ ተቀራርበው እና ተቀናጅተው እንሚሰሩም ገልፀዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኦቱካና ኦዳ በበኩላቸው መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በስንዴ ምርታማነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ያለው ተግባር ለሌሎች የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት በምሳሌነት ሊነሳ የሚችል ተግባር ነው ብለው፤ ተቋማት በጋራ ለአንድ ውጥን ዓላማ መስራት ውጤቱ አመርቂ መሆኑን ያረጋገጥንበት ጉብኝት ነው ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደጀኔ ሂርጶ ዩኒቨርስቲው ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትነ ለማሰደግ እሰራ ያለው ተግባር ይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት