የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ዝግጅት ጀመረ፡፡
***************************************************************
(ባሌ-ሮቤ ህዳር 19/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ተወዳዳሪዎችን ለመመልመል ዝግጅት መድረግ ጀመረ፡፡
ዝግጅቱን ያስጀመሩት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለስፖርት ቤተሰቡ ባደረጉት ንግግር ስፖርት ለሰው ልጆችን በማቀራረብ ወዳጅነትን የሚያጎናፅፍ፤ሰውንትን በመገንባት ጤንነትን የሚጠብቅ፤ሠላምን የሚሰብክ ትርፋማ ተግባር መሆኑን አንስተው፤ በውድድር ውስጥ ስፖርታዊ ወጉ ከማሸነፍ እና መሸነፍ በላይ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በመቀጠል ዛሬ የሚጀመረው ዝግጅት በአንድ በኩል የስፖርት እንቅስቃሴን ባህል ለማድረግ ሲሆን፤ በዋናነት ደግሞ የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ላይ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲን በተለያዩ የስፖርተ ዓይነቶች የሚወክሉ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ተወዳዳሪዎች ለመምረጥ መሆኑን ገልፀው፤ ዩኒቨርሲቲውን በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች በውጤት ለማጀብ ተወዳዳሮዎች ከወዲሁ ጠንክሮ መስራትና እና በስነ-ልቦና መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበው፤ በምንወዳደርባቸው የስፖርት ዓይነቶች ሁሉ በተወዳዳሪዎች ጥራት፤ ብቃትና ዲሲፒሊን፤ ቡድናችንን በመገንባት ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ለተሸለ ከፍታ ለመወዳዳር ከወዲሁ ማቀድ እንዳለባቸው ለተወዳዳሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዲን አቶ ተስፋዬ ዘውዴ በበኩላቸው የስፖርት እንቅስቃሴን ከውድድር እና መዝናኛ ባሻገር ባህላችን በማድረግ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፈጠር ፈይዳው ዘርፈ-ብዙ መሆኑን ተናግረው፤ ዘንድሮ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲን በከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ውድድር ተመርጠው ለሚወከወሉ ተወዳዳሪዎች ጽ/ቤታቸው ባለው አቅም ሁሉ ከጎናቸው መሆኑን ቃል ገብተው፤ ከፈተኛ ውጤት እንደሚጠብቁም አሳስበዋል፡:
በመክፈቻው የእግር ኳስ ውድድር በሰራተኞች ዘርፍ የአካዳሚክ ሰራተኞች ከፀጥታና ደህንነት ሰራተኞች ያለ ግብ በአቻ ውጤት ስለያዩ፤ በተማሪዎች በተደረገው የእግር ኳስ ውድድር እንጂነሪንግ ኮሌጅ ኮምፒቲንግ ኮሌጅን 3 ለ2 አሸንፏል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት










