የመደ ወላቡ የኒቨርሲቲ ከባሌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመሆን ከዞኑ ከተለያየ መስሪያቤቶች ለተወጣጡ ግንባር ቀደም ሴት ሰራተኞች የአመራር ብቃት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የመደ ወላቡ የኒቨርሲቲ ከባሌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመሆን ከዞኑ ከተለያየ መስሪያቤቶች ለተወጣጡ ግንባር ቀደም ሴት ሰራተኞች የአመራር ብቃት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

**************************************

(ባሌ-ሮቤ ህዳር 16/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)

የመደ ወላቡ የኒቨርሲቲ ከባሌ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ጋር በመሆን ከዞኑ ከተለያየ መስሪያቤቶች ለተወጣጡ 150 በላይ ግንባር ቀደም ሴት ሰራተኞች የአመራር ብቃት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አከዳሚክ፤ ምርምር፤ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረስብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ፤የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቆሙለት ዓለማ አንዱ የማህበረሰብ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው፤የኒቨርሲቲያችንም ያለውን የሰው ሀይል በመጠቀም በርካታ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በመስራት የአከባቢውን ህብረተሰብ በይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ ይህም የማህበረሰብ አገልግሎት ታግባራት ነው ብለዋል፡፡

የባሌ ዞን ሴቶች እና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሮውዳ ጃርሶ በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ሴቶች የማህበረሰቡ ግማሽ አካል እንደመሆናቸውና የተለያዩ ጫናዎችን ተቋቁመው በጥሩ የአመርር ቁመና እና የውሳኔ ክህሎት እንዲያዳብሩ በስራ ላይ ስልጠና ጉልህ ሚና እንዳለው ተናግረው፤ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችን አመራር ብቃት ለማሰደግ ይህን ስልጠና በመስጠቱ አመስግነዋል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መምህር ሁሳ አሎ ስልጠናው ሴቶች በአመራር ሚና ያላቸውን ልምድ እንዲያዳብሩና የውሳኔ ሰጪነት ክህሎት እንድያሳድጉ ለመርዳት የታለመ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፤ ስልጠናውም Transformational Leadership, Time Management እና Stress Management በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው ነገም ቀጥሎ እንሚስጥ ከወጣው መርሃ-ግብር ላይ ለመረዳት ተችሏል፡፡

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት