በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

*******************************************************

(ባሌ-ሮቤ ህዳር 19/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሴት ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዩኒቨርቲቲው መምህራን ተሰጠ::

በስልጠናው ላይ በመገኘት ንግግር የደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ፤ ምርመር፤ ቴልኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ ሴት ተማሪዎች የተለያዩ ለባቸውን ጫናዎች ተቋቅመው በትምህርታቸው የተሻሉ እና ተዋዳዳሪ እንዲሆኑ በማሳብ ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልፀው፤ ተማሪዎቹም ከስልጠናው የሚያገኙትን ትምህርት የእለት ተግባራቸው ውስጥ በማካተት በራሳቸው ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር በዛብህ አክለው ዩኒቨርሲቲው እንደ ሀገር የጋጠመውን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሸለ መልክ የትምህርት ጥራት ማሳያ እንዲሆን ተግተው እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ሊዲያ ትኩ በበኩላቸው በ2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴት ተማሪዎች ለተለያዩ ጎጂና አላስፈላጊ ድርጊቶች የተጋላጭነት ደረጃቸው ከፍ ያለ በመሆኑ መሰል የሕይወት ክህሎት ስልጠና እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀው፤ ጸ/ቤታቸውም በየጊዜው ሴት ተማሪዎችን የሚያስተምሩ፡ የሚያድግፉና የሚያነቃቁ ስልጠናዎችን በተለያዩ ግዜ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ እንስተው፤ ይህ የዛሬው ስልጠናም የዚሁ አካል ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን መምህርት ዮርዳኖስ ረሸድ ከሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል እና መምህር አብዱልወሃብ ጄይላን ከማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ሲሆኑ፤ ስልጠናው የሴት ተማዎሪዎችን ክህሎት እና እይታ ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀው፤ Self-awareness, Self-esteem, Peer-pressure, Assertiveness እና Goal setting በሚሉ ርዕሶች ላይ ያጠነጠነ መሆኑ ታውቋል፡፡

በመጨረም በዩኒቨርሲቲው ለመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ በስጦታ መልክ ተበርክቷል፡፡

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት