የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዝዳንት  የተከበሩ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ካምፓስ   የአከዳሚክ እና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር “የጋራ መግባባት ለሁለንተናዊ እድገት”  በሚል ርእስ ላይ ሰፊ ውይይት አደረጉ፡፡

(መወዩ፣ሻሸመኔ ኢትዮጵያ፣ ህዳር 09/2018ዓ.ም፣ ሕ.ዓ.ግ.ጽ.)

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዲሱ ፕሬዝዳንት  የተከበሩ ዶ/ር ብርሀነመስቀል ጠና ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ካምፓስ   የአከዳሚክ እና አስተዳደር ሠራተኞች ጋር “የጋራ መግባባት ለሁለንተናዊ እድገት”  በሚል ርእስ ላይ ሰፊ ውይይት አደረጉ፡፡

የውይይቱን መርሃ-ግብር እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ያስጀመሩት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሻሸመኔ ካምፓስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢፍቱ ገዳ የካምፓሱን ታሪካዊ ዳራ እና አሁናዊ ቁመና አቅርበው፤ ወደፊት ተቋሙን ወደ ተሻለ ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉትን ተግባራትም ለተሳታፊዎች አንስተዋል።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ  ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና   ውይይታቸውን የጀመሩት በትምህርት ሴክተር በተለያዩ ቦታዎች ለበርካታ ዓመታት በከፍተኛ ሀላፊነት የሰሩባቸውንና ያካበቱትን ልምድ እንዴት ተቋማትን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሻገር እንዳስቻላቸው በማጣቀስ እና በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲም እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል።

በውይይታቸውም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አብረው ስራ ከጀመሩት የሁለተኛ ትውልድ አቻ ተቋማት እኩል ስሙና ስራው በሚታወቅበት ደረጃ ላይ አለመሆኑን ማሳያ በማጣቀስ አብራርተዋል።

በንግግራቸውም ቤት በጋራ እንደሚገነባ ሁሉ  በአንድነት በመቆም ጠንካራ ተቋም መገንባት ይቻላል ብለዋል፡፡ በመሆኑም አብረን ሆነን ትንንሽ የሚመስሉ ግን ተጠራቅመውና ገዝፈው ተቋምን የሚጥሉ ችግሮችን በመለየት ፣ማረምና በማስተካከል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

 በካምፓሱ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሠራተኞች ሰፊ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ የተነሱት ነጥቦችም  የመማርሪያ ክፍሎች እጥረት  ከ ማስተማር፣  ችግር ፈች ጥናትና ምርምር፣ የተቀናጀ የማህበረሰብ አገልግሎት የግብአት ስርጭትና አጠቃቀምን እንዲሁም ዩኒቨርሲቲውን የኔ ነው ብሎ በባለቤትነት መስራት ጋር የተገናኙ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች በተሳታፊዎች ተነስተዋል።

በተመሳሳይ ተማሪዎችም በርካታ የመሠረተ ልማት፤ የማር-ማስተማር፤ የመልካም አስተዳደር፤ ወቅታዊ ሁኔታዎችና ሌሎች ዘርፍ ብዙ ጥያቄዎች ለአዲሱ ፕሬዚዳንት አንስተዋል።

በውይይቱ ላይ የተከበሩ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ካምፓሱን በሁለንተናዊ መንገድ ለማሳደግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ያላለሰለሰ ጥረት፣ በጋራ መስራት አንደሚያስፈልግ፣ በተለይም የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ፣የተግባር ትምህርትን ማጠናከር፤ተማሪዎችን ማብቃት፣ተማሪዎችን በእውቀት፣ክህሎትና ማብቃት ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ተሰብሳቢዎቹም ከአዲሱ ፕሬዝዳንት ጋር በመሆን ዩኒቨርሲቲያቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለመቀየርና ላቅ ወዳለ ከፍታ ለመውሰድ ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም በመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ሻሸመኔ ካምፓስ ሲሰሩ የነበሩ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ የተማሪዎች መኝታ፣ ቢሮዎች  የተጎብኙ ሲሆን፤ ከግንባታ ተቋራጮችም ጋር ውይይት ተደርጓል።

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት