በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ “የህፃናት ጥበቃ ቀን የመጫወት መብት ለሁሉም ህፃናት” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
************************
(ባሌ-ሮቤ ህዳር 11/2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ሕ.ዓ.ግ.ጽ)
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ “የህፃናት ጥበቃ ቀን የመጫወት መብት ለሁሉም ህፃናት” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የመወዩ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕ አቶ ኢሳ ሀሰን ህጻናት የነገ ሀገር ተረካቢና ተስፋ በመሆናቸው ሁሉም ዜጋ መብታቸውን ጠብቆ የማሳደግና የመንከባከብ ሀላፊነት እንዳለበት አስምረውበታል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ የሁኑት ወ/ሮ ሊዲያ ትኩ በበኩላቸው ሁሉም ሰው የህፃናትን የዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ህጎችና ድንጋጌዎችን በማክበርና በማስከበር ህፃናትን ጠብቆና ተንከባክቦ ማሳደግ አስፈላጊነትን አስረድተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ዩኒቨርሲቲያችን የህፃናትን መብት ለማሰከበር እየሰራ የሚገኘውን ተግባራትም አንስተዋል፡፡ በፕግራሙ ላይም ስለህፃናት መብት የሚያወሱ በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ትዕይንቶች የቀረቡ ሲሆን ብሮሸሮችም ለተሳታፊዎች ተሰራጭተዋል፡፡
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት







