መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና አርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና አርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
======
መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲና አርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት በተለያዩ የምርምር ዘርፎች በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙት የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ከሊልና የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ናቸው።
ዶክተር አህመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ፤ ዩኒቨርሲቲው ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉ ብቁና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለማፍራት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ችግር ፈቺና ማህበረሰብ ተኮር ምርምሮችን በተለያዩ የትኩረት መስኮች እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።
በተለይም በግብርና፣ ጤና፣ቱሪዝም፣ብዘሐ ህይዎት መስኮች የልህቀት ማዕከል ለመሆን እያደረገ የሚገኛውን ጥረት በችግር ፈቺ ምርምሮች ለማስተሳሰር ዕድል እንደሚፈጥር ተናግሯል።
ከኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት በዚሁ መሠረት መፈራረማቸውን ገልጸዋል።
ይህም ዩኒቨርሲቲው በዋናናነት ከኢንስቲትዩቱ ጋር በምርምር፣ በሥልጠናና በመረጃ ስርጭት በጋራ ለመስራት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የጎባ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጄይላን ቃሲም በበኩላቸው፣ ሪፈራል ሆስፒታሉ የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እየሰረ ነው።
ሪፈራል ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ እየሰጠ የሚገኛውን የጤና አገልግሎት ለማሳጥና በባለሙያዎቹ የሚካሄዱ የምርምር ተግባራት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር የፈጸሙት የመግባቢያ ሥምምነት ትልቅ አቅም እንደሆነ አመልክቷል።
የአርማወር ሐንሰን ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው ፤ኢንስቲትዩቱ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈራረመው የመግባቢያ ሰነድ በጤና ምርምርና በፈጠራ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
በተለይም በአገር በቀል ዕውቀት ላይ በመመስረት ለባህላዊ ህክምና በሚውሉ እጽዋት፣ ወባን ጨምሮ ትኩረት በሚሹ ሐሩራማና ሌሎች ተላላፊ በሆኑ የጤና ዘርፎች ላይ የምርምር ስራዎችን ላይ በትብብር እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።
በተለይ በባሌና አርሲ አካባቢዎች በብዛት የሚስተዋሉ የምግብ መውረጃ ቱቦ ከንሰርና የቲቢ በሽታ መከላከል ላይ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሥምምነቱ ዕድል የሚፈጥር ነው።
እንዲሁም በጤና የፈጠራ ስራዎችና በሌሎች የአቅም ግንባታ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመስራት እንደሚያስችልም ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ዶክተር አለማያሁ አባተ በሰጡት አስተያየት፣ የኒቨርሲቲው ከኢንስቲትዩቱ ጋር የተፈራረሙት ሥምምነት ወደፊት አብሮ ሊሰራባቸው የሚችሉ መሥኮችን ያመለከታ መሆኑን አስረድቷል።
የማህበረሰቡን ችግር መሰረት ያደረጉ ምርምሮችን በጋራ ለመስራት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ መሐመድ አማን ናቸው።
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በ1962 ዓ.ም የኖርዌይና ሲዊድን የህጻናት አድን ድርጅቶች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር የስጋ ደዌ በሽታን በጥልቀት ለመረዳትና የመከላከያ ክትባት ለመሥራት የሚረዱ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለማጠናከር የተቋቋመ ነው፡፡
ሮቤ ጥር 23/2016(ኢዜአ)
Credit: Muhe Bale

+5
All reactions:

Asrat Sime Bedada, Ahmed Hasan Dessiso and 217 others

3
8
Like

 

Comment
Share

Leave a Reply

Your email address will not be published.