በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 8 ኛው ብሄራዊ የምርመር ኮንፈረስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Madda Walabu University

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 8 ኛው ብሄራዊ የምርምር ኮንፈረንስ ‘’Research for innovation and socio economic development’’ በሚል መሪ ሀሳብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኮንፈረንሱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከግንቦት 22 እስከ ግንቦት 23 ,2014 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ዶ/ር ሀሰን ሽፋ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዘዳንት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ እንደገለፁት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በግብርና፣ በጤና ፣በማህበራዊ ሳይንስ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በስፖርት እና ሌሎች ዘርፎች በርካታ የጥናትና ምርምር ስራዎች እንደሰራ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው በተለይም በሶስት ዞኖች በባሌ፣ ምስራቅ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንዳከናወነ ገልፀዋል፡፡በኮንፈረንሱ 25 ያህል ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ ገልፀዉ ከ25ቱ ጥናታዊ ፅሁፎች ዉስጥ 23ቱ ጥናታዊ ፅሁፎች ከሌሎች ዩኒቨርሲቲ በመጡ ተመራማሪዎች የሚቀርቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኮንፈረንሱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል እንዳሉት እንደዚህ አይነት ጥናት እና ምርምር ኮንፈርንስ መካሄድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለዉ ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዎች በጥናትና ምርምር ዘርፍ ተሞክርዎቻቸዉን ለመለዋወጥ በር እንደሚከፈት ጠቅሳዉ በጥናትና ምርምር ክህሎት ዙሪያ ክፍተት ያለበት ጉዳይ ሊታሰብበት እና መሻሻል እንደሚኖርበት ገልፀዉ የጥናትና ምርምር ዉጤቶች ተሳታፊዉ ጋር መድርስ እንዳለባችዉ ብሎም አብሮ አቅዶ አብሮ ሠርቶ ዉጤቱን ተሳታፊዎች ጋር ማድረስ አለብን በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል፡

See Translation

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.