መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍት በድጋፍ አገፕ

መጻሕፍቱም በዋናነት የኢንጂነሪንግ ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ፣ የአካውንቲንግ፣ የኢኮኖሚክስ፣ የማርኬቲንግ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር፣ የቋንቋና ሥነልሣን ፣ የሥነፅሁፍ፣ ጂኦግራፊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢኮኖሜትሪክስ፣ ፊዚክስ፣ ኢኮሎጂ፣ ሂሳብ እና የመሳሰሉት ሲሆኑ ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጀምሮ እስከዩኒቨርስቲ ደረጃ ለመማሪያ እና ለማጣቀሻነት (reference) የሚያገለግሉ ናቸው::
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲም እነዚህን በውጭ ከሚገኙ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የተበረከቱለትን መጻሕፍት ከድጋፍ አድራጊዎቹ ጋር በመመካከር ለሌሎች ተቋማትም ድጋፍ ለግሷል::
በዚሁ መሠረት ዩኒቨርሲቲው በድጋፍ ካገፕው 15,000 መጻሕፍት ውስጥ በጦርነት ለተጎዱት ወሎ (4,000) እና ወልድያ (4,000) ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም 3,000 መፅሐፍትን ደግሞ ለአብርሆት ቤተመጻሕፍት አበርክቷል::
እነዚህን መጻሕፍት በመግዛትና ወደ አገር ቤት በማስመጣት ሂደት በገንዘብና ጊዜያቸውን በመሰዋት ከፍተኛውን ሚና የወጡት በአረብ ኤምሬቶች የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚያስተምሩት እነ ዶ/ር አብዱልወሃብ አደም ኢብራሂም ፣ ዶ/ር አብዮት ምንዳዬ ተሰማ ፣ ዶ/ር እዮብ ጥላሁን መንግስቴ ፣ መ/ር አብዱረዛቅ ከዲር ሀምዛ ፣ እንዲሁም ዶ/ር ጫንያለው ታዬ ናችው:: በተጨማሪም ለዚህ ድጋፍ እውን መሆን በአቡዳቢ የሚገኙ የኢትዮጵያውያን ኮሙኒቲ አባላት ድጋፍም ከፍተኛ ነበር::
የመጻሕፍት ርክክቡ ስነስርዓትም የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዲኤታ ወ/ሮ ብርቱኳን አያኖ እንዲሁም የመደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር በዛብህ ወንድሙ በተገኙበት በአብርሆት ቤተመጻሕፍት ተካሄዷል:: በተጨማሪም የወሎና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮች የአብርሆት ቤተመጻሕፍት ዋና አስተባባሪ ፣ የኢትዮጵያና የኦሮሚያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
Memorandum of Understanding (MoU) signed between Madda Walabu University (MWU) and Belarusian State University of Informatics and Radioelectronics (BSUIR)!
Memorandum of Understanding (MoU) signed between Madda Walabu University (MWU) and Belarusian State…
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄዱ! መስከረም 08/2015
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ከዩኒቨርሲቲው መምህራን/Academic staffs/ እና ሠራተኞች ጋር…
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከሚያስተምሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ግምታቸው 120 ሚሊዮን ብር የሚገመት 15,000 የተለያዩ መጻሕፍት በድጋፍ አገፕ
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከሚያስተምሩ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር…