የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም ለ14ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡

MWU Graduation
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓ.ም በ14ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ያስተማራቸውን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሁለት ተማሪዎች ዛሬ ሰኔ 11/2014 አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና እክስቴንሽን መርኀ ግብር በስምንት ኮሌጆች በኢንጂነሪንግ ፣ኮምፒቲንግ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በጤና ሳይንስ ፣ማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም በትምህርት እና ስነ- ባህሪ ኮሌጆች ስር ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና በብቃት ያጠናቀቁ ስድስት መቶ ዘጠና ስምንት/698/ ወንዶች እና ሁለት መቶ ሰላሳ አራት/ 234 / ሴቶች በአጠቃላይ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሁለት በ/932/ ተማሪዎቹን በመጀመሪያ ድግሪ ፕሮግራም ሰኔ 11/2014 አስመርቋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና መምህር እንዲሁም የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በላይ ሲመኔ እንዳሉት ተመራቂዎች ሀገራችን አሁን ላይ ያጋጠሟትን ችግሮች አልፋችሁ ለምርቃት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ተመራቂዎች ወደ ስራው ዓለም ሲገቡ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ በርካታ ችግሮች በማለፍ ስራ እድልን ከመንግስት ብቻ መጠበቅ ሳይሆን ስራ ፈጠራ ክህሎትን በማዳበር በተለያዩ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ ከተመራቂዎች ይጠበቃል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚሰጠዉ ግልጋሎት ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ ካለው ግልጋሎት ላቅ ባለ ሁኔታ ስራውን በጥራት እና በጥልቀት ማሳደግ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለእንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ስራውን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመማር ማስተማር በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ላይ በሰፊው ሲሰራ እንደቆየ ገልፀው ዩኒቨርሲቲው የአሁን ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ ሰላሳ ሰባት ሺ አምስት መቶ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁን ገልጸው በ2025 በሀገራችን ካሉ አምስት ችግር ፈች ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ ለመሆን መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እየሰራ እንደሚገኝም ዶ/ር አህመድ ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት ከክብር እንግዶች እጅ ተረክበዋል፡፡
May be an image of 9 people, people standing and indoor
May be an image of one or more people and people standing
May be an image of 9 people, people standing and indoor

Leave a Reply

Your email address will not be published.

X