በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ‘’የብሄራዊ ምክክሩ እድሎች እና ፈተናዎቹ’’ በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ፡፡

Taye

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ”የብሄራዊ ምክክሩ እድሎች እና ፈተናዎቹ” በሚል መሪ ቃል የሰላም ሚኒስቴር ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከዩኒቨርሲቲው ምሁራን ፣አስተዳደር ሰራተኞች፣ ተማሪዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀዳ ሲቄዎች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሄዷል፡፡

ውይይቱ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ስነ ስርዓት የተጀመረ ሲሆን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዘደንት ዶ/ር ሀሰን ሺፋ ለተጋባዥ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለብሄራዊ መግባባቱ ሀገራዊ ምክክሩ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም በያለበት በየደረጃው ውይይት እና ምክክር በማድረግ በሰላም ሁኔታ ላይ ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የውይይቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር አህመድ ከሊል እንዳሉት ትልቅ ሀገር አለችን ለዚህ ታላቅነታችን የሚመጥን አስተሳሰብ ለመገንባት የዉይይት መድረኮች በየደርጃዉ መዘጋጀት እና መካሄድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለዉ ገልፀዉ አለመግባባቶችን ለመፍታት የምነሄድበት መንገድ በመምረጥ መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲዉ ያለዉን ሠላም ካለፉት ሁለት አመታት በፊት ከነበረዉ አንፃር ሲታይ በእጅጉ መሻሻልም እንዳለ ገልፀዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና የብሄራዊ መጋባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታዬ ደንደኣ የባሌ ህዝብ ለውይይት እና ለምክክር አዲስ አይደለም በታሪክ እንደምናቀው ለስድስት ወራትህ ያህል ምክክር የተደረገባት ታሪካዊ ቦታና ህዝብ እንደሆነ ገልፀው ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ይኖርብናል ስንወያይ ልዩነቶቻችን ብዙ ያልሰፉ እንዳልሆኑ እድሉን ይሰጠናል በማለት የብሄራዊ ምክክሩን አስፈላጊነት ጠቁመዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ምሁራን ለሰላም መንገድ መጥረግ እና ማሳየት ላይ ያላቸው አበርክቶ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ዉይይት መድረኩ በመምህር አሚን ማማ እና ዶ/ር እንዳልካቸዉ ብረሀኑ በቀረቡ ሁለት መወያያ ሀሳቦች ላይ በተሳታፊዎች ምክክር ተደርጎባቸዋል፡፡

See Translation

 

 

 

 

 

+7

Leave a Reply

Your email address will not be published.