በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

training at MWU

በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ2014 ዓ.ም ለኮምፒቲንግ እና ኢንጂነሪንግ ተመራቂ ተማሪዎች ”Training on employability skills and job readiness “ በሚል ርዕስ ዙሪያ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡

የዴሊቨሮሎጂ ዩኒት ዲን ዶ/ር ተስፋዬ ግርማ ስልጠናው ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት ለስራ ቅጥር ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሁም ዝግጁ ሊያደርጓቸው በሚችል ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር አቅምና ችሎታዎቻቸውን እንዲሁም ክህሎታቸውን ለይተው በማወቅ ለስራ ቅጥር ብቁ የሚሆኑበትን ሁኔታ ለማመቻቸት አላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ገልፀው በዚህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ከአራት መቶ ሀምሳ /450/ በላይ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናውን በተገቢ ሁኔታ መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በክህሎትና ስራ ፈጠራ ሚኒስቴር ከደረጃ ዶትኮም እና ከመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፐሬዘዳንት ፅ/ቤት ጋር በትብብር የተሰጠ ስልጠና እንደሆነ ተናግረው በሁለተኛ ዙር ለጤና እና ህግ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናው እንደሚሰጥ ዶ/ር ተስፋዬ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ግንቦት 19/2014.

Leave a Reply

Your email address will not be published.