የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ15 ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡ ሐምሌ 13 /2015.

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ለ15ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ያስተማራቸውን አራት ሺ አስራ ሰባት /4017/ተማሪዎቹን ዛሬ ሐምሌ13/2015 አስመርቋል፡፡
ምርቃት ስነ ስርአቱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዬኒቨርሲቲው መምህራንን በማሰብ እና የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ በግብርና፤ በህክምና / Medicine/,በኢንጂነሪንግ ፣ኮምፒቲንግ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በግብርና ተፈጥሮ ሃብት፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በጤና ሳይንስ ፣ማህበራዊ ሳይንስ እንዲሁም በትምህርት እና ስነ- ባህሪ ኮሌጆች ስር ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና በብቃት ያጠናቀቁ አራት ሺ አስራ ሰባት/4017/ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለእንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ ለተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ የዛሬው የምርቃት ስነ ስርአት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 16 አመታት ጉዞ ውስጥ ልዩ ያደርገዋል፡፡ ዩቨርሲቲያችን መምህራኖች ላይ የደረሰው ድንተኛ የመኪና አደጋ በርካታ መምህራኖቻችንን ማጣታችን ደስታችንን የተሟላ አላደረገውም ብለው ዩኒቨርሲቲው መንግስት የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ያስቀመጠውን አቅጣጭ በመከተል በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንዳለ እና ከዚህም ውስጥ አንዱ የ 12 ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች አንዲሰጥ በተሰጠው መመሪያ መሰረት ተማሪዎች ተቀብሎ በስኬት አስፈትኖ በቀጣይም ከ አስራ ስምንት ሺ በላይ /18,000/ ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስፈተን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ ሮቤ ካምፓስ ፣ በጎባና እና ሻሸመኔ ካምፓሶች በመደበኛ፣ ኤክስቴንሽን እና ክረምት በቅድመ ምረቃ ፣ ማስተርስ እና ፒ.ኤች.ዲ ባጠቃላይ ከ ሀያ አራት ሺ በላይ/24,000/ ተማሪዎችን በማሰተማር ላይ እንደሚገኝም ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል፡፡
የእለቱ የክብር እንግዳ የባሌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልይ ሀገራችሁ ባላት አቅም እና ውስን ሀብት አስተምራ አዚህ አድረሳችኸለች እናንተም የያዛችሁት ሰርተፍኬት የመጨረሻ ግባችሁ እንዳልሆነ አውቃችሁ ስራን ሳትንቁ ስራ ፈጣሪ እንጂ ስራ ፈላጊ ባለመሆን ለሀገራችሁ እድገት አንድነት እና ሰላም መታተር ይጠበቅባችኋል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በዛይድ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት የአካባቢው ተወላጅ ዶ/ር አቢዮት ምንዳዬም በምርቃት ስነስርአቱ ላይ በመገኘት ልምድ እና ተሞክሮዎቻቸውን አጋርተዋል፡፡
በዕለቱ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ሽልማት ከክብር እንግዶች እጅ ተረክበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.