የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረብ ‘’አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን’’ የሚለውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል 4 ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘድንት ዶ/ር አህመድ ከሊል የዲንሾ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ገቢ ኡሲን ጨምሮ በርካታ ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና የዲንሾ ወረዳ ነዋሪዎች በተገኙበት በዲንሾ ወረዳ ሆራ ሶባ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እና የዲንሾ ወረዳ ግብርና ፅ/ ቤት በቅንጅት እንደተከናወነ የተገለፀ ሲሆን በእለቱ ከአሰራ አንድ ሺ/11000/ በላይ ችግኝ ተተክሏል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘደንት ዶ/ር አህመድ ከሊል እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የአካባቢ ጥበቃ እንደሆነ ገልፀው በተለይ ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት ዩኒቨርሲቲው ወደ ህብረተሰቡ በመግባት በአካባቢ ጥበቃ አና ቱሪዝም ዙሪያ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ያለ ሲሆን ይህ ዛሬ በዲንሾ ወረዳ የተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የስራው አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡አክለውም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን እንክብካቤውም በዛው ልክ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈው በተከላ መርሀ ግብሩ ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡
የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዘደንት ዶ/ር ሀሰን ሽፋ በበኩላቸው ለዚህ ለ4 ኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ከአስራ አንድ ሺ በላይ ችግኝ የተዘጋጀ ሲሆን ለዚህም ከ ስምንት መቶ ሺ ብር/800,000/ በላይ ወጭ እንደተደረገበት ገልጸው በቅንጅት በመስራት የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ ውጤት መምጣት ይኖርብናል ብለዋል፡፡

- 29 Jun
- 2022